Jump to content

ጣት

ከውክፔዲያ
አምስቱ ጣቶች በግራ እጅ ላይ

ጣት በሰዎች እንዲሁም በሌሎች እንስሶች እጅ እና እግር ጫፍ ላይ የሚገኝ አንጓ ያለው ተንቀሳቃሽ የሰውነት ክፍል ነው። አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በእያንዳንዱ እጆቻቸው ላይ አምስት ጣቶች አላቸው። አንዳንድ ጊዜ ግን በአፈጣጠር ችግር ቁጥሮቻቸው ሊጨምሩ እንዲሁም በአደጋ ምክንያት ቁጥሮቻቸው ሊያንሱ ይችላሉ። የመጀመሪያው ጣት አውራ ጣት ተብሎ ይጠራል። በመቀጠልም ሌሎቹ አመልካች ጣት (በተለምዶ ሌባ ጣት) ፣ የመሃል ጣትየቀለበት ጣት እናም ትንሿ ጣት (በተለምዶ ማርያም ጣት) በመባል ይታወቃሉ።

ባለ አምስት ሬይ የፊት እግሮች የምድር አከርካሪ አጥንቶች ከፋይሎጀኔቲክ የዓሣ ክንፎች ሊገኙ ይችላሉ።